St. Raguel
Home
About Us
News
Events
Contact
Login
አማርኛ
EN
ለሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን በሙሉ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ዓመታዊ | Event Details
አማርኛ
English
None
ለሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን በሙሉ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ዓመታዊ
ስለ ኩነቱ ማብራሪያ
ለሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እና ምእመናን በሙሉ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋገራችሁ አሸጋገረን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ዓመታዊ የበዓለ ሢመት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! አዲሱ ዘመን የቆሸሸውን በአዲስ የምንተካበት፣ ያደፈውን የምናጥብበት ጸዓዳውን ልብስ የምንለንስበት እና ለመንፈሳዊ ሕይወታችን አዲስ ውሳኔ የምንወስንበት የጸጋ ዘመን ነው። አምላካችን እግዚአብሔር ያለፈውን ዓመት መዓትና መከራ አሳልፎ፣ በምሕረቱና በቸርነቱ አዲሱን ዓመት ባርኮ ስለሰጠን ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ንግሥተ ሳባ ጥበብን ፍለጋ ከሀገሯ ተነስታ ኢየሩሳሌም ተሻግራ ከጠቢቡ ሰሎሞን ጥበብን ተቀብላለች ለጣቷም እንቁ ተቀብላ ሕገ ኦሪትን ሥርዓተ መንግሥትን ታቦተ ጽዮንን እስከ ሌዋውያን ካህናት ለመምጣት ምክንያት ሆናለች ጥበብን በፈለገችው ንግሥት ጥበብን ልንሻበት አዲስ ዘመን ተሰጥቶናል ። የምሕረትን ሸማ የንስሐን በር ልንቀበልበት ለአባታችን ኖኅ የሰላምን የልምላሜን የተስፋን የብርሃንነትን የገለጠችውን የርግቧን ወይራ ተመልክተን አዲሱን ዓመት ንስሐ የምንገባበት ራሳችንን ለተቀደሰው አገልግሎት የምናበቃበት ነው የስሙ ትርጓሜ ብርሃነ እግዚአብሔር የተባለው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አራተኛ ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው በመጽሐፈ ሄኖክ እንደተጠቀሰው ቅዱስ ራጉኤል የብርሃናትን አካሄድ የሚመራ፣ ከዋክብትንና ጨረቃን ከነበራቸው መስመር እንዳይወጡ የሚያዝዝ የከዋክብት አለቃ ነው። በዚህች ዕለት አምላካችን እግዚአብሔር ለቅዱስ ራጉኤል ታላቅ ክብሩንና ሢመቱን የሰጠበት፣ ለሰው ልጅ ምሕረትና ጸሎትን የሚያሳርግ የብርሃን መልአክ አድርጎ የሾመበት ዕለት ነው። ቅዱስ ራጉኤል ሰዎችን ከክፉ ነገር የሚጠብቅ፣ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የምሕረት ጸሎትን የሚያደርስ፣ እንዲሁም ለቅዱሳን አባቶቻችን በራእይ እየተገለጠ ምሥጢርን የተናገረ ታላቅ መልአክ ነው። የቅዱስ ራጉኤልን ተራዳኢነትና ጥበቃ አይልየን፤ ሰንበት ትምህርት ቤታችንን፣ ሀገራችንንና ሕዝባችንን በሰላምና በፍቅር ያጽናልን። ይኸው አዲስ ዓመት የአንድነት፣ የታማኝ አገልጋይነት እና የላቀ መንፈሳዊ ዕድገት የሚገለጥበት እንዲሆንልን እንመኛለን።
ወደ ኩነቶች ተመለስ
የኩነቱ ዝርዝር
ቀን
September 11, 2026
ሰዓት
12:00 AM
ቦታ
ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤ/ክ አንቀጸ ብርሃን ሰ/ት/ቤት